ማነው ምንትስ?

ፋሲል ሆቴል፡፡ ሶሎሞን ገባ፡፡ አዜብ ሰለመችው፡፡ ሰላም አላት፡፡ ጂን አዘዘ፡፡ አዜብ አመጣችለት፡፡ ማን እንደ አዙካ!

ሙዚቃ ቢጤ አለ፡፡ ‹‹አለው አለውና ሲደብረው ተኛ›› ይላል ዘፈኑ፡፡ ‹‹ሶል›› ያዳምጣል፣ በልቡ አዙካን ያላምጣል፡፡ አይ አዜብ!

አዜብ ጥሩ ልጅ ነች፡፡ ካወቃት ቆይቷል፡፡ እዚቹ ቤት፡፡ የዛሬ ሦስት ዓመት፡፡ አልተለወጠችም፡፡ ሰው አይለወጥም? ያ’ደራ ዕቃ!

ያኔ …. የመጀመሪያው ቀን ሲያውቃት ስታውቀው ትዝ ይለዋል፤

‹‹አዙዬ››
‹‹ወዬ››
‹‹አይደል ስምሽ?››
‹‹አዎ ነብሴ»
‹‹ለመሆኑ ብዬሻለሁ?»
‹‹ምኑን ነብሴ?»
‹‹ደስ እንደምትዪኝ?»
‹‹አንተ ብቻ አይደለህም!»
«እህሳ?»
‹‹ብዙ ሰው ይለኛል፡፡»
‹‹ኧረ?»
‹‹ግርምሽ ይሙት፡፡»
‹‹ግርምሽ ደግሞ ማነው?»
‹‹ባሌ!»
‹‹መች ያገባሽው?»
‹‹ሳሚ የተወኝ ለታ፡፡»
‹‹ሳሚ ለምን ተወሽ?»
«በኤርሚ ጠረጠረኝ»
«ኤርሚ ደግሞ ማነው?»
‹‹ወዳጄ!»
‹‹እንዴት እንዴት ይወድሻል?»
‹‹እንደ አስፋው፣ አንደ ታዬ፣ እንደ ፍቅሩ፣ እንደ አምባዬ፣ እንደ ጌትሽ፣ እንደ በቅሽ፣ እንደ…»
‹‹በቃ በቃ ተዪው፡፡»
‹‹ታዲያ ለምን ጠየቅከኝ?»
‹‹ዝም ብዬ ነው፡፡ ይልቅ ቁጭ በይ፡፡»
‹‹ምን ይዤ?»
‹‹ደስ ያለሽን፡፡»

ኮኛክ ይዛ መጣች፡፡
አብረው አመሹ አብረው አደሩ፡፡ ተፋቀሩ… እና ዛሬ…

ጂኑን ይጠጣል፡፡ ሙዚቃ ያዳምጣል፡፡ አዜብን ያላምጣል፡፡ አይ አዜብ! ሐሳብ ፈረሰኛው ቼ!

«አዜብ ምንድነች?»
‹‹ሸርሙጣ?»
‹‹ሸርሙጣ ምንድነው?»
‹‹አዜብ!»
«ምኗ ሸረሞጠ?»
«ሁለመናዋ!»
‹‹ለመሆኑ እዚህ ለምን መጣሁ?»
‹‹ልዝናና፡፡»
‹‹ከማን ጋር?»
«ከአዙካ፡፡»
‹‹አዙካ ምንድነች?»
«ሸርሙጣ፡፡»
‹‹እኔስ?»
‹‹’ማነው ማንትስ”
“ይህን ያለው ማነው?»
‹‹ጸጋዬ ገ/መድኅን፡፡»

Membership Required

ይህ ጽሁፍ ለለደስታ ደንበኞች ብቻ ነው። እንዲህ ያሉ ጽሁፎችን ለማገዝ በወር $5 ወይም በዓመት $50 በመደገፍ ደንበኛ ይሁኑ።

Already a member? Log in here

Subscribe to Ledesta

New writing in your inbox. English and Amharic.

Support Ledesta

Or contribute directly to sustain the publication.

Donate
አጋራ
Scroll to Top