የት ሄጄ ልፈንዳ!

A panicked man clutches his head while calm figures around him point at him

«ኮሎኔል ዘለቀ፣ በዚህ ድፍረትህ ይገድሉሃል!»

«ለምንድነው የሚገድሉኝ?»

«እንዴ በገዛ ቤታቸው?! በገዛ አልጋቸው…?!»

«እንዴ ሚስታቸኮ አይደለችም! ልጃቸው ናት»

«እኔ አላውቅም ግን ይገድሉሃል!»

«እንዴ መግደል እንዲህ ቀላል ነው እንዴ?»

«ሽጉጥ አውጥቶ መተኮስ መሰለኝ!»

«ማለቴ ህግ የሚባል ነገርኮ አለ»

«እንዴ ታዲያ እሱ ከመግደል ጋር ምን ያገናኘዋል?»

«ምን ማለትህ ነው?»

«ሰምተኸኛል? ይገድሉሃል!»

«እንዴ እንዲህ ማሰብ የማይችሉ ናቸው እንዴ?»

«መግደል ራሱ’ኮ ማሰብ ነው»

«አልገባኝም»

«አስበህ ትገድላለህ ወይም ገድለህ ታስባለህ?»

«በመካከል ግን መግደል አለ»

«እየገደልክም ልታስብ ትችላለህ! ሀሳብ አይቆምም»

«በናትህ አትፈላሰፍ! ንገረኝ!»

«እኔ አትፈላሰፍ የሚለኝ ሰው አልወድም»

«በላ አንተም ደግሞ ግደለኝ»

«አሁንማ ሌላ ሰው ይገድልልኛል። ምን አደከመኝ!»

«እና አንተም ተባባሪ ልትሆን ነው ማለት ነው?»

«አንድ ሽጉጥ በቂ ነው፤ ሌላ ሽጉጥ አያስፈልግም»

«እና ኮሎኔሉ ይገድሉሃል ነው የምትለኝ?!»

«አዎ!»

«መቸ የሚያደርጉት ይመስልሃል?»

«አላማከሩኝም»

«ታድያ እንደሚገድሉኝ እርግጠኛ የሆንከው ለምድነው?»

«ስለሚገድሉህ!»

«አንተ እሳቸውን ብትሆን የምታደርገውን እያሰብክ ነው?»

«አይደለም፤ እሳቸው እኔን ሆነው ያሰቡትን ነው»

«እንዴት አወቅክ?»

«ቢያንስ ራሴን አውቃለሁ!»

Membership Required

ይህ ጽሁፍ ለለደስታ ደንበኞች ብቻ ነው። እንዲህ ያሉ ጽሁፎችን ለማገዝ በወር $5 ወይም በዓመት $50 በመደገፍ ደንበኛ ይሁኑ።

Already a member? Log in here

Subscribe to Ledesta

New writing in your inbox. English and Amharic.

Support Ledesta

Or contribute directly to sustain the publication.

Donate
አጋራ
Scroll to Top